የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤ የትኩረት ነጥቦች
ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ፍትሐዊ አገልግሎት በመስጠት መልካም አስተዳደርን ማስፈን
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን አምርሮ በመታገል የተጠያቂነት ሥርዓትን ማረጋገጥ
የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማስፋት የአገልግሎት ቅልጥፍናን ተቋማዊ ባህል ማድረግ፤
የንግድ ምዝገባና ፈቃድ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና ማሻሻል፤
በእሁድ ገበያዎችና መንግስት በገነባቸው የገበያ ማዕከላት የምርት አቅርቦትን በማስፋት የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትና መከላከል፤
ስለቅሬታ ምንነትና አቀራረብ ምን ያህል የውቃሉ?
ቅሬታ ማለት የትኛውንም አይነት አገልግሎት እንዲሰጥ በህግ በተቋቋመ የመንግስት መ/ቤት ላይ ማንኛውም ተገልጋይ የሚያቀርበው በአገልግሎት ያለመርካት መግለጫ ሲሆን ስህተቶች ስለመፈፀማቸው በተለያዩ መንገዶች የሚደርሱና ምላሽ የሚሚሹ ጥቆማዎችንና አስተያየቶችን ያጠቃልላል፡፡
ዓላማዎች
- 1በመንግስት ተቋማት ውስጥ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና አስተዳደራዊ በደልን መከላከል፣
- 2በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ በተገልጋዮች ለቀረቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት፣
- 3የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ለመጠበቅ የሚያግዙ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማገልገልና ለተጠቃሚዎች አለመርካት መንስኤ የሚሆኑ ስህተቶችን ማረም፡፡
- 4መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ የሚያጋጥሙ ችግሮችና መንስኤዎችን በመለየት እንዲቃለሉ/እንዲወገዱ/ ማድረግ፡፡
መርሆዎች
- 1ቅሬታ የማቅረብና የመደመጥ እድል መስጠት
- 2የቅሬታ አቀራረብን ቀላል ማድረግ፣
- 3ለቀረበው ቅሬታ ፈጣን ምላሽ መስጠት
- 4የቅሬታ አቀራረብ ስርዓቱን ውጤታማ ማድረግ፣ሃቀኛ፣ገለልተኛ፣ሚዛናዋ ሆኖ መገኘት፣